HOME PAGE / ABOUT
To ensure an effective implementation of the country’s short and long term construction programs and projects in terms of time, finance and quality through building, project management capacity of key actors of project implementers and thereby sustain the ongoing rapid development of the country.
To see the countries’ construction project performance excellent by 2020.
Work continuously for sustainable result improvement
የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር ለኢንስቲትዩቱ በማቋቋሚያ ደንቡ የተሰጡት ዋና ዋና ሥልጣንና ተግባራት፡-
1. ተወዳዳሪ የሆነ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት አቅም ለመገንባት የሚረዱ የፖሊሲ ሀሳቦችን፣ ስትራቴጂዎችንና መርሀ-ግብሮችን ማመንጨት እና በመንግሥት ሲፈቀዱም ተግባራዊ ማድረግ፣
2. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ክፍተቶችን በመለየት ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መስጠት፣
3. በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ለሚሠማሩ ባለሙያዎች ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖር እና ብቃትና ክህሎት ላይ የተመሠረተ የሥራ ሥምሪት ተግባራዊ እንዲደረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
4. የቴክኖሎጂ አቅም እንዲፈጠርና እንዲሸጋገር የሚያስችሉ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዘዴዎችን በመለየት በኢንዱስትሪው ውስጥ የማስረጽ ሥራ መሥራት፣
5. በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ባለቤቶች፣ ሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች በጋራና በተናጠል የሚፈፀሙ ተግባሮችን በመለየት ወጥ የሆነ የፕሮጀክት አሠራር ሥርዓት መቅረጽና ማስተዋወቅ፣
6. በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት መስክ የማማከር አገልግሎት መስጠት፣
7. ለኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት አቅም ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ማደራጀትና እንደ አስፈላጊነቱ ለተጠቃሚዎች ማሠራጨት፣
8. ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ክህሎትና ዕውቀት እንዲስፋፋና እንዲዳብር የጥናትና ምርምር ተግባራትን ማከናወን፣
9. ለኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ክህሎት ዕድገት አጋዥ በሆኑ የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚዘጋጁ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፣
10. ተመሣሣይ ዓላማ ካላቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ከሚገኙ የመንግሥትና የግል ተቋማት እና የሙያ ማህበራት ጋር ትብብር ማድረግ እና በግል ተቋማት መካከልም ተመሳሳይ ትብብር እንዲደረግ ማበረታታት፣
11. በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አፈጻጸም ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ የምርጥ ተሞክሮዎች ጥናት ማካሄድና በዘርፋ ተመሳሳይ ተግባር የሚያከናውኑትን መደገፍ፣
12. ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የኮንስትራክሽን ፕሮግራምና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ክህሎት ማሳደግን በተመለከተ በመተባበር የመሥራት፣ በጋራ የምርምር ሥራዎችን የማካሄድ እንዲሁም በዘርፉ የሀገር ውስጥ የምርምር አቅም እንዲጠናከር ማገዝ፣
13. ለሚሠጣቸው አገልግሎቶች በመንግሥት በሚወሰን ተመን መሠረት የአገልግሎት ዋጋ ማስከፈል፣
14. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን ማከናወን ናቸው፡፡